አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ኮምቦልቻ ወረዳ ግምቱ 2 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ትናንት ሌሊት አንድ ግለሰብ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው።
በፖሊስ ከተያዙት ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ሲጋራዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የዝናብ ላስቲክ ሸራዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
የመጋዘኑ ባለቤትም ሆነ ተከራዩ ግለሰብ ለጊዜው ከአካባቢው መሰወራቸውንና ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!