Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገረ ስብከቱ ለተፈናቃዮች የምግብ እህልና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው ደሴ ለተጠለሉ ወገኖች ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ እህልና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የሰሜን ሽዋ ዞን ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቃ ጥበብ አባቡ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ፥የህወሓት የሽብር ቡድን በከፈተው ጦርነት ምንም የማያውቁ ጨቅላ ህጻናትና አቅመ ደካሞች ለሞት፣ለረሃብና እንግልት ተዳርገዋል።
የሽብር ቡድኑ እኩይ ሴራ የሚያሳዝንና በፈጣሪም ይቅር የማይባል ክፉ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀገረ ሰብከቱ ከህዝበ ክርስቲያኑ፤ ከባለሃቶችና ከሌሎች አካላት ባሰባሰበው ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጭ የምግብ እህልና ቁሳቁስ ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል።
ከድጋፉ መካከል 500 ብርድ ልብስ፣ 200 ፍራሽ ጨምሮ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ማካሮኒና የተለያዩ አልባሳት እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
“የተፈናቃዮቹ ሁኔታ እንቅልፍ የሚነሳ በመሆኑ በቅርቡ ተጨማሪ ድጋፍ እንድናደርግ ያስገድደናል” ያሉት ስራ አስኪያጁ ፥ በቀጣይም ከጎንደርና አፋር ለተፈናቀሉ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version