Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሲሪስ አፕል ጁስ 100% መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲሪስ አፕል ጁይስ 100% የተሰኘው ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በሲሪስ አፕል ጁይስ ውስጥ 100% ስለተገኘ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል፡፡
ይሄ ምርት የዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ያስጠነቀቀ ሲሆን፥ በተመሳሳይ የሲሪስ አፕል ጁይስ አምራች የሆነው የደቡብ አፍሪካ የምግብና የመጠጥ አምራች ምርቱ ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በውስጡ በእንዳለ በመግለጽ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ነው ያሳሰበው፡፡
በመሆኑም ህብረተሰባችን የሲሪስ አፕል ጁይስ 100% ምርት በሀገራች ገበያ ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ ምርቱን እንዳይጠቀም ያስጠነቀቀ ሲሆን÷ ምርቱን በማንኛውም አጋጣሚ ገበያ ላይ ሲገኝ በፌዴራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጥቆማ እንዲቀርብ ባለስልጣኑ ጠይቋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version