አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢቢሲ ግሎባል በለንደን በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የ2021 የዓለም ሚዲያ ሽልማት ጋዜጠኛ ዘይነብ ባዳዊ አሸናፊ እንደሆነች ተገለጸ፡፡
ቢቢሲ ግሎባል ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ለሽልማት ያበቃቸውን በተራኪ ፕሮግራማቸው ጥልቀት እና ሚዲያውን ለማጉላት የተጠቀሙትን የፈጠራ ስልት፣ አዳዲስ የሚያቆጠቁጡ ጣቢያዎችን የሚጠቀሙበት ሥልት እና በዓለም አቀፍ አድማጭ ተመልካቾቻቸው ልብ ውስጥ ያላቸው ቀረቤታ እና ቦታ በመገምገም መሸለሙ ተጠቁሟል፡፡
ዘይነብ ባዳዊ ትውልደ ሱዳናዊት ስትሆን በሁለት ዓመቷ ከወላጆቿ ጋር ወደ ለንደን ማምራታቸው ነው የታወቀው፡፡
ዘይነብ የሱዳን እና የእንግሊዝ ዜግነት ሲኖራት በቢቢሲ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ላይ በምትሰራቸው ሪፖርቶች፣ ዜናዎች እና ፕሮግራሞች እውቅናን አትርፋለች፡፡
ከዘይነብ በተጨማሪም “ማላሪያ ኖ ሞር ዩኬ” ፣ “ሌዲስ ሩል ዘ ሮድ”፣ “አታክ ኦቭ ዘ ኪለር ቶሜቶስ”፣ “ፒች ዘ ፊዩቸር”፣ “ትራንዚሽኒንግ ቱ ኤ ክሊክ ኢኮኖሚ”፣ “ፓወር ፈርዘር ቱጌዘር”፣ “ፕሌይ እስቴሽን 5”፣ “ሳምሰንግ”፣ “ላይቭ ፍሮም አውስትራሊያ ” እና “ፌዴክስ” የተሰኙ በጤና፣ በሥርዓተ ጾታ፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርትና ኢንዱስትሪ፣ በባህሪ ለውጥ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በመዝናኛ፣ እንዲሁም በመሪነት እና ፈጠራ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እና የሚዲያ ፕሮግራሞች ተሸላሚ እንደሆኑ ወርልድ ሚዲያ ግሩፕ ገልጿል፡፡
በዓለማየሁ ገረመው