Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከባንግላዲሽ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከባንግላዲሽ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር፣ የባንግላዲሽ ባለሃብቶች ሊሳተፉባቸው የሚችሉ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት እድልና አማራጮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድልና አማራጮች በጋራ የማስተዋወቅ ስራን መስራት በዋናነትና በስፋት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች የሚጠቀስ መሆኑን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version