አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ልዑክ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚዘጋጀውን የአለም አቀፉን የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ ዝግጅት በሚመለከት በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።
8ኛው አለም አቀፉ የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ ከግንቦት 27 ቀን 2014 ጀምሮ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ከ2 ሺህ በላይ እንግዶች የሚስተናገዱበት ኮንፈረንስ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ዝግጅት እያደረገች ነው።
በዝግጅቱ ዙሪያ የአለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ተወካዮች ከቴሌኮም ልማት ኮንፈረንሱ አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር በአዲስ አበባ እየተወያዩ ነው።
የኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ፥ ኮንፈረንሱን እውነተኛ የአፍሪካ መድረክ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።
ጉባኤው ኢትዮጵያ ራሷን ለአለም የምታስተዋውቅበት መድረክ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፥ ለጉባኤው ስኬትም ሁሉም ርብርብ እንዲያደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
8ኛው አለም አቀፉ የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚካሄድ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!