አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተመራው ልዑክ በዶዶላ ከተማ በግንባታ ላይ ያለውን አዳሪ ትትምህርት ቤት ጎበኘ፡፡
የኦሮሚያ ክልል በክልሉ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች እንዲማሩባቸው ከሚስገነባቸው 7 ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የዶዶላ ትምህርት ቤት ግንባታው ከ90 በመቶ በላይ ደርሷል ተብሏል፡፡
ክልሉ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን÷ ከነዚህም ውስጥ የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እና ኢፋቦሩ በተሰኘ መርሃ ግብር የሚገነባቸው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የሚጠቀሱ ናቸው።
ይህ ተሞክሮ አገራዊ እንዲሆን በማሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም የሁለቱ ከተሞች አስተዳደሮች የተሳተፉበት ጉብኝት ተደርጓል።
አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ በተያዘው ወር መጨረሻ ተማሪዎችን ይቀበላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።
በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!