አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዚምባብዌ ማዕድን ማውጫ ስፍራ በደረሰ አደጋ 20 ሰዎች በአፈር ሲቀበሩ የሁለት ሰዎች ህይዎት አልፏል።
ማዕድን አውጭዎቹ ከመዲናዋ ሐራሬ በስተምዕራብ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ በስራ ላይ እያሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው ተብሏል።
ሰራተኞቹ ከረቡዕ ምሽት ጀምሮ በአፈር ውስጥ መቀበራቸውንም ነው ፖሊስ የገለጸው።
አሁን ላይም በህይዎት ያሉ ሰዎችን የመፈለግ ስራው መቀጠሉንም አስታውቋል።
በዚምባብዌ በማዕድን ማውጫ ስፍራዎች ከደህንነት መሳሪያ እጥረት ጋር በተያያዘ አደጋ በተደጋጋሚ እንደሚደርስ ይነገራል።
ባለፈው አመት ከመዲናዋ ሃራሬ አቅራቢያ በደረሰ አደጋ 24 ማዕድን አውጭዎች መሞታቸው ይታወሳል።
ዚምባብዌ የማዕድን ውጤቶች ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጯ ሲሆኑ፥ ወርቅን ጨምሮ የዳይመንድ እና ፕላቲኒየም ባለቤት ናት።
ምንጭ፦ አልጀዚራ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision