አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የጋምቤላ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማትና ሰራተኞች ምስጋናና እውቅና ሰጠ፡፡
በክልሉ ያለውን የፋይናንስ ስርዓት ለማሻሻል እንዲሁም የ10 ዓመት መሪ አቅድ ለማዘጋጀት ግንባር ቀደም የሆኑ አካላትን ተቋሙ አመስግኗል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ ኡቦንግ ኡቶው ባለፈው በጀት አመት የቢሮው ሰራተኞች በታቀደው እቅድ በመመራት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንዲሰራ ያደረጉት ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሰራተኞችን ለማመስገንና እውቅና ለመስጠት ያስፈለገው አዲሱ መንግስት ያስቀመጣቸውን የልማት ዕቅዶች ካለፉት አመታት በተሻለ መልኩ በተነሳሽነት ሃላፊነታቸውን ለመወጣት እንዲችሉ ለማበረታት ነው፡፡
ለክልሉ የፋይናንስ መሻሻል አስተዋፅዖ በማድረጉ ረገድ አመራሩ የሚያደርገው ተሳትፎ ከፍተኛ በመሆኑ ባለፈው የበጀት አመት የክልሉ መንግስት የቀድሞ የፋይናንስ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኡሞድ በሰሩት በጎ ተግባር ተሸልመዋል፡፡
ላለፉት በርካታ አመታት ክልሉ በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ክፍተቶች የታዩበት በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ሲገጥሙ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ ከተቋማትና ከፋይናንስ ሰራተኞች ጋር በመመካካር የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደው ለውጥ ማምጣት እንደተቻለ መናገራቸዉን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!