Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በወረባቦ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ. ቢ.ሲ) በወረባቦ ወረዳ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእለት እርዳታ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፋ ተደረገ።
ከፌደራል እና ከክልል ምግብ ዋስትና እና አደጋ መከላከል ኮሚሽን የተገኘውን የእለት እርዳታ ለ13 ሺህ 552 የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደርጓል።
የወረባቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኅላፊ ሙአዘ መሐመድ ፥ የድጋፉ ተጠቃሚዎች በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው እና በባለፈው ዓመት በአንበጣ ሰብላቸው ለወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለተጎጂዎች ድጋፍ ከተደረጉት መካከል 7 ሺህ 550 ኩንታል ስንዴ፣ 650 ኩንታል ነጭ ዱቄት፣10ኩንታል ሩዝ 650 ብርድልብስ እና አልሚ ምግብ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
61 ሺህ ለሚሆኑ የቤተሰብ አባላት 11ሚሊየን 250 ሺህ ብር የሚያወጡ የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል።
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
የፎቶ ምንጭ፡- የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version