Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል የመማር ማስተማር ሂደቱ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የ2014 የመማር ማስተማር ሂደት በኦሮሚያ ክልል በይፋ ተጀመረ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ÷ በቢሾፍቱ “ከራ ሆራ መዋለ ሕፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት” በመገኘት የ2014 የመማር ማስተማር ሂደት በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡

በክልሉ ከ 9 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር መመዝገባቸውም ተገልጿል፡፡

ዶ/ር ቶላ ÷ የመማር ማስተማር ሂደቱ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ፕሮቶኮልን ያከበረና ተማሪዎች በኮቪድ 19 እንዳይያዙ ጥንቃቄን መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድም አስገንዝበዋል፡፡

በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የንፅሕና አገልግሎት ለማሟላት በተደረገው እንቅስቀሴ የኢፋ ቦሩና ቡኡ’ራ ቦሩ ትምህርት ቤቶች በባለሐብቱ እና በመንግስት ትብብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ዶ/ር ቶላ ጠቁመዋል፡፡

በክልል እየተገነቡ ከሚገኙ 3 ሺህ የቡኡ’ራ ቦሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህዎቹ ተጠናቀው የትምህርት መሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች እንደተሟላላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version