Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ካፒቴን በህረዲን አብዱ በደሴና ኮምቦልቻ መጠለያ ጣቢያ በመገኘት ጉብኝት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ለተፈናቀሉ ዜጎች ከሰሙት በላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

ካፒቴን አህመድ አባድር 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ጤፍ ፣ ሩዝና የዕለት ደራሽ ምግቦች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር አህመድ የሱፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎቹ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አየር መንገዱ የሀገሪቱን አርማ ይዞ በየሀገሩ ሲዘዋወር የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው ማለታቸውን ከኮምቦልቻ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version