አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለጤና ሚኒስቴር 50 አምቡላንሶችን ድጋፍ አድርጋለች፡፡
ድጋፉ የተደረጉት አምቡላንሶች የተሟላ መሣሪያ ያላቸውና 250 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ናቸው ተብሏል፡፡
ልገሳው የተደረገው በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቀይ ጨረቃ ማህበር በኩል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ የመጀመሪያዎቹ ሰባት አምቡላንሶች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የአምቡላንሶቹ የትራንስትፖርት ወጪም በማህበሩ እንደሚሸፈን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!