Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ44 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት ከ44 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን ÷የገቢ ኮንትሮባንድ 43 ሚሊየን 12ሺህ 9 ብር፤ ወጪ ደግሞ 1ሚሊየን 437ሺህ 851ብር ግምት አላቸው፡፡

አቃቂ ቃሊቲ እና ሞያሌ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ላይ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሊያዙ መቻላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከልም የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ ተሽከርካሪ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ አደንዛዥ እጽ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version