የሀገር ውስጥ ዜና

በአየር ኃይል የምዕራብ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ውጥታማ ለሆኑ መስመራዊ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ተሰጠ

By Feven Bishaw

October 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ኃይል የምዕራብ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ውጥታማ ለሆኑና የመቆያ ጊዜአቸውን ለሸፈኑ መስመራዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች የማዕረግ እድገት ተሰጠ።

የምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ቸርነት መንገሻ ÷ ለተሿሚዎቹ ማዕረግ ካለበሱ በኋላ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ሽብርተኛ ለመደምሰስ በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምድቡ ለትውልድ የሚተላለፍ ጀብድ ፈፅሟል ።