አዲስ አበባ፣ ጥቅምት1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ኃይል የምዕራብ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ውጥታማ ለሆኑና የመቆያ ጊዜአቸውን ለሸፈኑ መስመራዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች የማዕረግ እድገት ተሰጠ።
የምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ቸርነት መንገሻ ÷ ለተሿሚዎቹ ማዕረግ ካለበሱ በኋላ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ሽብርተኛ ለመደምሰስ በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምድቡ ለትውልድ የሚተላለፍ ጀብድ ፈፅሟል ።
የምድቡ ሰራዊት “ሰው እስኪደክመው ይሰራል ወታደር ግን ለአገሩ ለቆመለት አላማ ህይወቱ እስኪሰዋ ይሰራል “የሚለውን ብሒል የአላማ ፅናትን ፥ ቅንነትን ፥ ታማኝነትንና ቆራጥነትንና ፍፁም ሕዝባዊነትን የበለጠ በመላበስ ምድቡ የሚሰጣችሁን ግዳጅ መወጣት ይጠበቅባችኋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ ለሠው ሐብት ልማት ኮሎኔል አበበ ኃይሉ÷ በቀጣይ ብቃታችሁንና ክህሎታችውን ተጠቅማችሁ ዜጎችን ሰላምና ጤና በመንሳት የኢትዮጵያን ደስታና ተስፋ ለመንጠቅ የሚጥረውን አሸባሪ የህዋሃት ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ዝገጁነታችሁን ማጠናከር ይገባችኋል ብለዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!