Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሪፐብሊኩ የጥበቃ ሀይል አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ)የቆይታ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሪፐብሊኩ የጥበቃ ሀይል አመራርና አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ።
የማዕረግ ዕድገቱ የተሰጣቸው ከባለ ሌላ ማዕረግተኞች እስከ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ናቸው።
ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱትና የስራ መመሪያ የሰጡት የመከላከያ የህብረት የሰው ሀብት ዋና መምሪያ ሀላፊ ሜጀር ጄነራል ሀጫሉ ሸለመ÷ በመስዋዕትነትና በጠንካራ የግዳጅ አፈፃፀም ላገኛችሁት የማዕረግ ዕድገት እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
ተሿሚዎችም ባገኙት የማዕረግ ዕድገት ለበለጠ ግዳጅ ዝግጁ በመሆን ያስመዘገቡትን ድል ለማስቀጠል የበለጠ መትጋት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ተሿሚዎች በበኩላቸው÷ የተሰጣቸው የማዕረግ ዕድገት ለሀገራቸው የበለጠ ስራ ለመስራት የሚያነሳሳ በመሆኑ ለቀጣይም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version