Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ከአሜሪካ የፓርላማ እና ኮንግረስ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ከአሜሪካ የፓርላማ እና ኮንግረስ አባላት ጋር ተወያዩ።

አፈ ጉባኤው ከሴናተር ጀምስ ኢንሆፊ እና ከኮንግረስ አባሉ ስቲቨን ሆርስፎርድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።

በተያያዘም አፈ ጉባኤው ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ቢስሊ ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

Exit mobile version