የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ከወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጋር የሥራ ርክክብ አደረጉ

By Meseret Awoke

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሰላም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ብናልፍ አንዷለም ከወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለአዲሱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ራዕይና ዕሴት እንዲሁም ሲከናወኑ የቆዩ ተግባራት ላይ ገለፃ ተደርጓል፡፡

አዲሱ ከፍተኛ አመራርም የተቋሙን መልካም ዕሴቶች በማጎልበትና አዳዲስ ሀሳቦችን በመጨመር እንሰራለን ማለታቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!