Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ዊንዶውስ 11” የዕይታ ማሻሻያዎች እና አዲስ “የማይክሮሶፍት ስቶር” ያካተተ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዊንዶውስ 11” በስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል፡፡

በዚህም “የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም” ተጠቃሚዎች ከፈረንጆቹ ጥቅምት 5 ጀምሮ ኮምፒውተሮቻቸውን በ“ዊንዶውስ 11” በነፃ ማዘመን እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ማዘመኛው ቀድሞ የሚለቀቀው ለዘመናዊ ኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ሲሆን÷ እስከ ፈረንጆቹ 2022 ድረስ ግን ሁሉም “የማይክሮ ሶፍት ዊንዶውስ” ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ተጠቅሷል፡፡

“ዊንዶውስ 11” የዕይታ ማሻሻያዎች እና አዲስ “የማይክሮሶፍት ስቶር” ያካተተ ነውም ተብሏል፡፡

“ዊንዶውስ 11” የመጣው “ዊንዶውስ 10” ተግባር ላይ ከዋለ ከስድስት ዓመት በኋላ እንደሆነና “ዊንዶውስ 11” ጉልህ ለውጥ እና ዝመና ይዞ እንደመጣም ነው የተመላከተው፡፡

ሆኖም “ከዊንዶውስ 8” ወደ “ዊንዶውስ 10” በተደረገው ሽግግር ላይ ከታየው ጉልህ የአጠቃቀም ለውጥ አንፃር “ከዊንዶውስ 10” ወደ “ዊንዶውስ 11” የተደረገው ሽግግር እምብዛም የጎላ እንዳልሆነ ነው የዊንዶውስ ስራ አስፈፃሚ ጂኦፍ ብላበር የተናገሩት፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ማይክሮሶፍት ካምፓኒ ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ የ ”ዊንዶውስ” ተቃሚዎች አሉት፡፡ ዘገባው የ ሲ ኤን ኤን ነው፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

Exit mobile version