አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ሶሊና ሆምስ ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የማዕድ ማጋራት እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በፈፀመው ወረራ በርካቶች ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው ለእንግልት እና ስቃይ ተዳርገዋል።
የሶሊና ሆምስ ሥራ አስኪያጅ እና ባለቤት አቶ ዐቢይ ወልደየስ÷ ለተፈናቃዮች የማዕድ ማጋራት እና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጭ የሆነበት ይህ ድጋፍ ከሶሊና ሆምስ ቤተሰቦች የተሰበሰበ ነው ተብሏል።
የተፈናቀሉ ወገኖችን መደገፍ እና መጠየቅ እንደሚገባ የገለፁት አቶ ዐቢይ÷ ሌሎችም በሚችሉት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ድጋፍ ከተደረገላቸው ወገኖች መካከል ወይዘሮ የትምወርቅ በጋሻው እና ወይዘሪት ገነት ቦጋለ ይገኙበታል።
ሶሊና ሆምስ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው÷ መንግሥት በአሸባሪ ቡድኑ ላይ በአፋጣኝ እርምጃ ወስዶ ወደቀያቸው እንዲመለሱ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!