የሀገር ውስጥ ዜና

በአየር ኃይል ምስራቅ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ምስጉን ለሆኑ የምድቡ ሰራዊት አባላት ማዕረግ ተሰጠ

By Feven Bishaw

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፥ 2014 ዓ.ም( ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምስራቅ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ምስጉን ለሆኑና የመቆያ ጊዜያቸውን በጥሩ ወታደራዊ ዲሲፒሊን ለሸፈኑ የምድቡ ሰራዊት አባላት ማዕረግ ሰጠ።

ለተሿሚዎቹ ማዕረግ በማልበስ የስራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ኮ/ል አበበ ለገሰ ፣ አየር ምድቡ ህግን በማስከበር ዘመቻ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍና የህወሃት አሸባሪ ቡድንን በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈፅሟል ብለዋል።