አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲን የካንሰር ህክምና ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ለማሟላት ለሚደረገው ጥረት መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ገለጹ።
ሚኒስትር ዲኤታው በ2 00 ሺህ ብር ወጪ የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን የገባለትን የካንሰር ህክምና ማዕከል ትላንት ሲጎበኙ እንዳሉት በኢትዮጵያ ውስጥ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በተለይ የካንሰር ስርጭት እየጨመረ ይገኛል።