የሀገር ውስጥ ዜና

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ነገ ይከበራል

By Feven Bishaw

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣መስከረም 30፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ነገ ይከበራል፡፡

ቀኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች ፣በወታደራዊ ካምፖች ፣ኤምባሲዎች እና በሌሎች ተቋማት ተከብሮ እንደሚውል የአዲስ አበባ ምክር ቤት ገልጿል፡፡