Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ነገ ይከበራል

አዲስ አበባ፣መስከረም 30፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ነገ ይከበራል፡፡

ቀኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች ፣በወታደራዊ ካምፖች ፣ኤምባሲዎች እና በሌሎች ተቋማት ተከብሮ እንደሚውል የአዲስ አበባ ምክር ቤት ገልጿል፡፡

የዘንድሮ የሰንደቅ ዓላማ በዓል ከሌላው ጊዜ ለየት ባለ ሁኔታ ኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞዋን በአዲስ ምዕራፍ መንግስት መስርታ በጀመረችበት ማግስት መሆኑ ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ልዩ ትርጉም ያለው ነው ብሏል፡፡

በመሆኑም በእለቱ ሁሉም በዓሉን ሲያከብር ሰንደቅ ዓላማችን የመልማት፣ የተስፋና የመስዋእትነት ምልክት መሆኑን አግልቶ በማውጣት ሊሆን ይገባል ሲል ምክር ቤቱ መልዕክቱን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version