Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በግንባር ተገኝተው የፀጥታ ኃይሉን አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ተገኝተው የጸጥታ ኃይሉን አበረታትተዋል፡፡
ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚከናወኑ ስራዎችን በሙያ ለማገዝና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጥናትና ምርምሮች ለመስራትም ከፍተኛ አመራሮቹ ቃል ገብተዋል፡፡
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም መስርተው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ስራዎችን መስራታቸውም ተገልጿል፡፡
የመስክ ምልከታና ጉብኝቱ ችግሮችን ተረድቶ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው፡፡
በጉብኝቱ የጎንደር ፣ ባህርዳር ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ታቦር፣ ወሎ፣ ወልድያ እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆኑ÷ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ዘርፈ ብዙ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለቀጣይ ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሻሻል ፋይዳ ያላቸውን ድጋፎች እንደሚደርጉ የፎረሙ ፕሬዚደንት ዶክተር ታፈረ መላኩ አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version