አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ34ተኛ ዙር የተማሪዎች ምርቃትን አስመልክቶ የስድስተኛው ዙር የማህበረሰብ ሳምንት መዝጊያ ፕሮግራም አከናውኗል።
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት በተደራጀ መልኩ ላለፉት 6 ዓመታት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው ከሚሰጣቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች ውስጥ ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ኢ መደበኛ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርትን ጨምሮ ተቋሙን ከማህበረሰቡ ጋር የሚያስተሳስሩ ስራዎች በጥቂቱ የሚጠቀሱት ናቸው።
በእለቱም ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር በአቡሎ ቀበሌ የ3 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ግንባታን አጠናቆ አስመርቋል።
በተጨማሪም 340 የሚሆኑ በኢ መደበኛ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል ።
በአቤል እንዳቅሙ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
36,873
People Reached
726
Engagements
Boost Post
371
1 Comment
11 Shares
Like
Comment
Share