አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዛይሁዋንና ከቻይና የኢኮኖሚ እና የንግድ ጉዳዮች ሚኒስተር ኮንስላር ሩ ያንግ ዪ ሃንግ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ግንኙነት በፕሮሞሽን፣ በአፍተር ኬር ፕሮግራም እንዲሁም በተለያዩ የልምድ ልውውጦች ማጠንከር፣ ከቻይና ባለሃብቶች ጋር ተደጋጋሚ የትስስር መድረኮችን በመፍጠር ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡