አዲስ አባባ፣መሰከረም 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ሰራተኛ ጋር በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም ሰራተኛው በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ አሉ ያለቱን የአሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአደረጃጀት ችግሮች ለሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ፕሮፌሰሩ ከሰራተኞች የተነሱትን ሀሳቦች እንደ ግብዓት በመውሰድ እና መፍትሄ በመስጠት በቅንጅት የተሻለ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የትምህርት ሴክተሩ የፓለቲካ መስሪያ ቤት ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቋቋመ ሴክተር በመሆኑ የፓሊቲካ አመለካከታችንን ወደ ጎን ትተን በተቋሙ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ተቋም በመሆኑ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚጠበቅም መግለጻቸዉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!