አዲስ አበባ፣መስከረም 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አል ባስይራ ባስኑር የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አርባ ምንጭ ገባ፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘዉዴን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የBusiness to Business ግንኙነት ለመፍጠር እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየት የኢንዶኔዥያ ባለሀብቶች በዞኑ በተለያዩ የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
አምባሳደሩ በተፈጥሮ ወደታደለችው አርባምንጭ ከተማ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ÷አከባቢው በጣም ውብ ከመሆኑ ባሻገር ለም አፈር ያለዉ በመሆኑ ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ምቹ አከባቢ ነው ብለዋል፡፡
በአምባሳደሩ የተመራው ልኡክ በሚኖረው ቆይታ ከጋሞ ዞን አስተዳደር እና ከአርባምንጭ ከተማ ንግድ ማህበራት ዘርፍ ምክር ቤት ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጋሞ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!