አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ሽብርተኛው ትህነግን አስወግዶ በግፍ የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ቀያቸው ሊመልስ እንደሚገባ በምዕራብ ጎንደር ዞን ነዋሪ የሆኑ የታሪክ እና የሥነ ዜጋናሥነ ምግባር መምህራን ገለጹ።
የታሪክ መምህር የሆኑት አቶ ጥላሁን አስራት÷ የትላንት አያቶቻችን ኢትዮጵያን ከቅኝ ግዛት ነጻ አውጥተው የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ ትልቅ ዋጋ መክፈላቸውን አንስተው፣ በወቅቱ ባንዳዎች ደግሞ ጣሊያን ኢትዮጵያን እንድትገዛ አብረው በመሰለፍ ተባብረው ነበር ብለዋል፡፡
መምህሩ አያይዘውም ሽብርተኛው ትህነግ የፈጸመው ክህደት ተመሳሳይ የባንዳነት ተግባር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አሸባሪው በአማራ ክልል ያደረሰው አሰቃቂ ድርጊትና መፈናቀል የከፋ እንደሆነና የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀዬአቸው በመመለስ ሥነ ልቦናቸውን ልንጠግን፣ ሀዘናቸውን ልንካፈል፣ ያለንን ልናካፍል እና እስኪቋቋሙ መንግሥት ያላሰለሰ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
እንዳልካቸው ደማስ የተባሉ የታሪክ መምህር ደግሞ ÷ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዓልሞ የተነሳው የሽብር ቡድኑ ብቻ ሳይሆን ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው ምዕራባዊያንም ጭምር መሆናቸውን ሁሉም ሊረዳ ይገባል ብለዋል፡፡
የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህሩ ሰይድ መብሬ በበኩላቸው ÷ ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር ዜጎች በግፍ ከመፈናቀል ባለፈ የሚከፈለው ሰብዓዊ ኪሳራ ነውና በአዲስ የተዋቀረው መንግሥት ለነገ ሳይል ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲቋጭ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!