Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ሱዳን የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከ600 ሺህ በላይ ዜጎች ለጉዳት ተጋለጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን ከግንቦት ወር ጀምሮ እየተስፋፋ በሄደው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ቢያንስ 623 ሺህ ያህል ዜጎች ለጉዳት መጋለጣቸው ተገለፀ፡፡

በአደጋው በርካቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው በመሸሽ ላይ መሆናቸውም ነው የተመላከተው፡፡

በሀገሪቷ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎም ወንዞች ሞልተው ከሀገሪቷ 10 ግዛቶች ሥምንቱ ላይ የመጥለቅለቅ አደጋ ማድረሱም ተመላክቷል፡፡

የእርዳታ ሠራተኞች ጀልባዎችንና ታንኳዎችን በመጠቀም 75 በመቶ የሚሆነውን ተጎጂ የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ መሆን እንደቻሉ ተጠቅሷል ፡፡

ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር ጀምሮ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡና በዚህም ሳቢያ የሀገሪቷ ዜጎች ለረሃብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ያመላከተው አልጀዚራ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version