አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጣልያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር እና የትብብር ሚኒስትር ማርያ ሰረኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህም በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ፣ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ፣ ድርድር እና ቀጣይ የጋራ ትብብር ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በነገው ዕለትም “ኢንካውንተርስ ዊዝ አፍሪካ 2021” የኢነርጂ ኮንፈረንስ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!