Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ስካይ ያለ ዲሽ ሳህን መስራት የሚችል የቴሌቪዥን ስርጭት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የእንግሊዝ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት ስካይ የሳተላይት ሳህንን አስፈላጊነት በማስወገድ ስርጭቶችን በበይነ መረብ በኩል የሚያስተላልፍ የቴሌቪዥን ብሮድካስት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ይፋ የተደረገዉ ሲስተም እንደ ሳምሰንግ እና ሶኒ ካሉ የቴሌቪዥን ስርጭቶች ጋር በቀጥታ ፉክክር ውስጥ እንደሚስገባው የተቋሙ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡
አዲሱ የስርጭት ሲስተም የሳተላይት ሳህንን ለመሰቀልና ለማዉረድ የሚዉለዉን ጊዜ በመቆጠብ ለተጠቃሚዎች ምቹ መሆኑንም ነው ባለሙያዎች የገለጹት፡፡
ስካይ ግላስ የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ይህ ሲስትም ዶልቢ አቶምስ የተባሉ የድምፅ መጨመሪያና መቀነሻ የተገጠመለት ሲሆን÷ ቲቪዎችን ያለ ስፒከሮች ማዳመጥ ይቻላል ተብሏል፡፡
ሲስተሙ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ዘመናዊ የሚባለዉ የቴሌቪዥን ስርጭት መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳና ስሮንግ ተናገረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version