አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የዲያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አለባቸው ደሳለኝ እንደገለጹት÷ በተለያዩ ሀገራት የምንገኝ የዲያስፖራዎች ለሰራዊታችን ከምናደርገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በአካል በመገኘት ደም መለገሳችን ለሰራዊታችን ያለንን ድጋፍ ያሳያል ብለዋል።
በተለያየ ምክንያት ከሀገር ርቀን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ሰራዊታችን ደማችንን ከደሙ ጋር በመቀላቀል ያለንን ድጋፍ ለማሳየትና በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ከጎኑ መሆናችንን ለማሳየት ያለመ በጎ ተግባር መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
የመከላከያ የደም ባንክ ሀላፊ ሻምበል ዶክተር ብርሀኑ ካሳዬ በበኩላቸው ÷ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወገኖች ለሰራዊታችን እያደረጉት ለሚገኘው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አመስግነው ÷ ሀገር አቋርጠው በመምጣት ከስጦታዎች ሁሉ የላቀውንና ህይወት የሆነውን ደም መለገሳቸው ለሰራዊታችን ከፍተኛ ሞራል እንደሚሆነው ገልፀዋል።
በደም ልገሳው ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ አባላት ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!