Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ህጻናትን ለማሳደግ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር 15 ህጻናትን ተረክቦ ለማሳደግ በገባው ቃል መሰረት ህጻናቱን ተረክቧል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጻናቱን የተረከበው ከሜሪጆይ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል መሆኑ ተገልጿል፡፡

15ቱን ህጻናት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና 4 ተጠሪ ተቋማት በጋራ እንደሚያሳድጓቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ምህረት ምናስብ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መስፍን አስፋ÷ ህጻናቱን ለማሳደግ ስንረከብ የሚሰማን የመንፈስ እርካታ ወደር የማይገኝለት ነው ያሉ ሲሆን ÷ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ከአብራካችን እንደወጡት ልጆቻችን ተንከባክበን ለማሳደግ ቃል እየገባለን፤ ህጻናቱ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት በማምጣት ሀገር ተረካቢ ዜጋ እንዲሆኑ አደራ ለማለት እንወዳለን ብለዋል፡፡

የሜሪጆይ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ÷ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍና እገዛ ምስጋና አቅርበው የመረዳዳት ባህላችን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version