Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ልዩ የስነ-አዕምሮ ጤና አገልግሎት የህክምና ማዕከል በጅማ ዞን ማረሚያ ቤቶች ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27 ፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከልና የጅማ ዞን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በመተባበር ልዩ የስነ-አዕምሮ ጤና አገልግሎት የህክምና ማዕከል በጅማ ዞን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ግቢ ዉስጥ ተከፈተ፡፡
በማዕከሉ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጤና ኢንስቲትዩት ም/ፕሬዚደንት ዶክተር ኤልያስ ዓሊ እንደተናገሩት፥የስነ-አዕምሮ ጤና አገልግሎት አሰጣጡን በማሳደግና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የምርመራ ማዕከሉ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የሚሰጠው አገልግሎት የተሟላ እና ቀጣይነት ያለዉ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ግብዓቶችን ድጋፍ በማድረግ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡
በጅማ ዞን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የማረምና የማነጽ ሥራ ሂደት አስተባባሪ ዋና ሳጂን አብዱራዛቅ ያሲን በበኩላቸዉ ከዚህን በፊት ታራሚዎችን ለስነ-አዕምሮ ጤና ምርመራ ምልልስ በሚደረግበት ጊዜ ተጠርጣሪዎች ከህግ ጥላ ስር የማምለጥ፤ተጨማሪ ወንጀል የመስራት ሙከራ መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
አሁን ማእከሉ በጊቢ ዉስጥ መከፈቱ ችግሩን መፍታት ማስቻሉንና አላስፈላጊ የሆኑ የወጪ፤የጊዜ እና የጉልበት ብክነትን ለመቀነስ የሚረዳ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የጅማ ጤና ኢንስቲትዩት የክሊኒካል ቺፍ ዳይሬክተር ዶክተር ፈቲያ አወል፥ የተጀመረዉን ሥራ ለማጠናከር ያለንን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ለዉጤታማነቱ እንሰራለን ብለዋል፡፡
በተለይ በዘርፉ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን በአግባቡ በመጠቀም አገልግሎቱን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል ቁርጠኛ ነን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version