አዲስ አበባ፣ መስከረም 27 ፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርቡ ሙያዊ ስነ ምግባራቸውን በተላለፉ ፖሊሶች ድብደባ የደረሰባት ሰሚራ መሐመድ በተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከል ስራ ጀመረች።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሙያዊ ስነ ምግባራቸውን በተላለፉ ፖሊሶች ድብደባ የደረሰባት ሰሚራ መሐመድ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት በጀመረው የተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከል በቋሚነት ስራዋን ጀምራለች።
ሰሚራ በክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት በመገኘት በአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቃል በገቡት መሰረት የስራ ቅጥር ውል በትላንትናው ዕለት በመፈጸም ስራ መጀመሯን ከከተማዋ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!