አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ምስረታው የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የጎላ ሚና እንዳለው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ገለጹ፡፡
የደሴ ከተማ ቅርንጫፍ ኢዜማ ፓርቲና የደቡብ ወሎ ዞን አብን ጽህፈት ቤት አመራሮች÷ በመንግስት ምስረታው ሂደት ተፎካካሪ ፓርቲዋች መካተታቸው የዲሞክራሲ ምህዳሩ እየሰፋ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋ፡፡
የኢዜማ ደሴ ቅርንጫፍ ሊቀመንበር አቶ አይነቱ ሀይሉ እንደገለጹት÷ ዛሬ የተመለከትነው ነገር ደስ የሚያሰኝ እና በኛ ዘመን መሆኑ የሚያኮራ ነው፤ የዲሞክራሲ ልምምዱንም ቢሆን ከፍ የሚያደርግና ሀገራዊ እድገትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡
ከተፎካካሪ ፓርቲም ይሁን ከገዢው ፓርቲ ወደ አስፈጻሚ አካላት የመጡ ግለሠቦች መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃት እንደሚወጡ እምነቴ ነውም ብለዋል፡፡
የአብን የደቡብ ወሎ ዞን ጽህፈት ቤት የፓለቲካ ጉዳዮች ሀላፊው አቶ ሰለሞን ፈንታው በበኩላቸው÷ የሚቀሩ ተግባራት እንዳሉ ሁነው መንግስት አካታች ሂደት መከተሉ ለዲሞክራሲ ስርአት መሻሻሉ መንገድ ከፍች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሀገርን እጣ ፈንታ በጋራ ለመወሰንም ትልቅ አስተዎጽኦ አለው ሲሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!