Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ የ “ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሆን ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ አንድ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደሚያስፈልጋት በቀረበው ትንታኔ መነሻነት የቀድሞ ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ የ “ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሆን መወሰኑን ዩኒቨርስቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
ተጠሪነቱም ለትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ለፓርላማው ቀርቦ በአዋጅ መደንገጉ ተገልጿል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ዩኒቨርሲቲው ልዩ ባህርይን ተላብሶ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version