Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አዲሱ መንግስት ለሰላም ማስፈንና የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተመሰረተዉ መንግስት የኑሮ ዉድነትን ማረጋጋትና ሰላም ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ የሰጡ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
አዲስ የተመሰረተው መንግስት ሰላምን ከማስፈን ቀጥሎ የዋጋ ንረትንና የኑሮ ውድነት ማረጋጋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
ሰላም ከሁሉም ነገር በላይ መሆኑን የገለጹት አስተያየት ሰጭዎቹ፥ የኑሮ ዉድነትም የሁሉም ህዝብ የልብ ትርታ በመሆኑ መንግስት መፍትሄ ሊያበጅለት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም መንግስት ሰላምን ለማስፈን እና የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከል በሚያደርገው ጥረት ሁሉ ከጎኑ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
ጉዳያቸው ውስብስብና ተደራራቢ መሆኑን የጠቆሙት አስተያየት ሰጭዎቹ፥ የተመረጠዉ መንግስት የህዝብ ጥያቄዎችን እንደሚያሳካ እምነት አለን ብለዋል፡፡
ዶክተር አብይ አህመድ በቀጣይ በመንግስታቸው መሰራት አለባቸዉ ብለው ያስቀመጧቸዉ ጉዳዮች ለኢትዮጵያ ህዝብ አንገብጋቢ ጉዳዮች በመሆናቸዉ÷ እኛም ፍትህ የምንፈልግ አካላት ፍትሃዊ አሰራርን መከተል አለብንም ነው ያሉት፡፡
ሌብነትን እንደሚዋጉ አስምረው መግለጻቸዉ ተገቢ መሆኑን ያነሱት አስተያየት ሰጭዎቹ፥ ኢትዮጵያውያን ተስፋ ሳንቆርጡ ችግሩን በጋራ ለመታገል ጥረት ማድርግ እንዳለባቸውም አመለክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version