የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ም/ቤት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

October 06, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

የምክርቤቱ ፕሬዚደንት ሼክ ሱልጣን አማን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትህነግ አሸባሪ ቡድን ያፈናቀላቸውን ወገኖቻችንን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለመመልከትና ድጋፍ ለማድረግ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪ ሙስሊምና ክርስቲያኑም እኛ እያለን ህዝባችን አይራብም፤ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እስከሚመለሱና መንግስት አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የህልውና ዘመቻውን በአፋጣኝ እርምጃ ተወስዶ የማቋቋም ስራ እንሰራለን ብለዋል።

የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሰይድ የሱፍ÷ ጦርነቱ በድል ባለመጠናቀቁና በመራዘሙ የተፈናቃይ ቁጥር በመጨመሩ ከከተማው አቅም በላይ ሁኗል።

በአንድ ክፍል ከ150 በላይ ሰዎች ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን÷ ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አከላት የሚደረገው እርዳታ አጥጋቢ ባለመሆኑ ጦርነቱ ጊዜ ተሠጥቶት ወደመጡበት የሚመለሡበት መንገድ እንዲመቻች ምክረ ሃሳብ መስጠታቸዉን ከደሴ ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!