የሀገር ውስጥ ዜና

መገናኛ ብዙሃን አሸባሪው ህወሓት በወረራ የፈጸመውን ግፍና በደል በጥፋቱ ልክ ለሌላ ዓለም ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል-አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

By Meseret Demissu

October 05, 2021

አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ አሸባሪው ህወሓት በወረራ የፈጸመውን ግፍና በደል በጥፋቱ ልክ ለሌላው ዓለም ማህበረሰብ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ተመለከተ።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል።

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በመድረኩ እንዳሉት ፥ አሸባሪው ቡድን በክልሉ በገባባቸው አካባቢዎች ንጹሃን  ከመግደል ባለፈ  ዜጎች በእድሜ ዘመናቸው ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በመዝረፍ  ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ ፈጽሟል።

”የሚጭነውን ጭኖ የቀረውን በማውደም የአማራን ህዝብ አንገት ለማስደፋትና እድሜ ልኩን በድህነት እንዲማቅቅ ለማድረግ የያዘውን ግብ ለማሳካት ተንቀሳቅሷል” ብለዋል።

የቤት እንስሳትን አርዶ በመብላት፤ ያልቻለውን በጥይት በመግደል አርሶ አደሩ ዳግም ወደ እርሻ እንዳይመለስ የሚችለውን ሁሉ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ለዘመናት የተገነቡ ተቋማትን በማውደምና በመዝረፍ ህብረተሰቡ የጤና፣ የትምህርት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዳያገኝም እንዲሁ።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የአሸባሪ ቡድኑን የጥፋት ተግባር ባለማውገዙ በማይካድራ የጀመረውን የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ በአጋምሳ፣ ጭናና ሌሎች አካባቢዎች በመድገም የአሸባሪነት ጥጉን ማረጋገጡን አቶ ግዛቸው  ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!