የሀገር ውስጥ ዜና

አንድነት ፓርክ ከቅዳሜ እስከ ረቡዕ ድረስ ለጎብኚዎች ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ

By Tibebu Kebede

February 06, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድነት ፓርክ ከመጭው ጥር 30 እስከ የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለጎብኚዎች ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ።

በእነዚህ ቀናት ፓርኩን ለመጎብኘት ትኬት የቆረጡ ጎብኚዎች ከሀሙስ የካቲት 5 ቀን ጀምሮ ጉብኝታቸውን ማከናወን እንደሚችሉም ፓርኩ ገልጿል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የመጡ እንግዶችን የአንድነት ፓርክን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ለማስጎብኘት ዝግጅት ተጠናቋል።