Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተዓማኒ ምርጫ በማድረግ የደረስንበት ይህ አዲስ ምዕራፍ በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ረጅም የመንግስት አስተዳደር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዓማኒ ምርጫ በማድረግ የደረስንበት ይህ አዲስ ምዕራፍ በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ ምዕራፍ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት የሃገራት መሪዎች፣ ከፍተኛ የሃገራት የመንግስታት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደር እንዲሁም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት መካሄዱ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ያላቸውን ተስፋ እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያላቸውን አክብሮት እና ፍቅር በሞቀ ስሜት መግለጻቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version