Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት በደመቅ ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መስቀል አደባባይ ሲደርሱ ከመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመስቀል አደባባይ መምጣታቸውን ይጠባበቅ የነበረው ህዝብ በከፍተኛ ስሜት በጭብጨባ ተቀብሏቸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ የሕዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን፥ በበዓለ ሲመቱ ላይ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ አምባሳደሮች፣ የውጭ አገር ተቋማት ሃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሦስት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተመረጡበት ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ያሰሙት ንግግር በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚወደስ ታሪካዊ ንግግር እንደሆነ አይዘነጋም።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version