Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለአፍሪካዉያን ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ የአንድነትና የሃገራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ እጅጉን አስፈላጊ ነዉ-ዩዌሪ ሙሴቪኒ

አዲስ አበበ፣ መስከረም 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙት የዩጋንዳዉ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህንን መልዕክት የማስተላልፈው የዩጋንዳን ህዝብ ወክየ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነው ብለዋል።
ለአፍሪካዉያን ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ የአንድነትና የሃገራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ እጅጉን አስፈላጊ ነዉም ሲሉ ዩዌሪ ሙሴቪኒ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version