አዲስ አበበ፣ መስከረም 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር አብይ አሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ መሪዎች መልካም ምኞታቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ዶክተር አብይ አህመድ የመልካም ምኞት መልእክታቸውን ያስተላለፉት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝደንት ሼክ ክሃሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን፣ የኤሚሬቱ ምክትል ፕሬዝደንት ጠቅላይ ሚኒስትርና የዱባይ መሪ ሼክ ሞሃመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም እንዲሁም የሃገሪቱ ልኡልና የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንም መሆናቸውን የኤሚሬትስ ዜና አገልግሎን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን