አዲስ አበባ፣ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በዛሬው የመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም ነው አዲስ አበባ የገቡት፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በርናባስ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን