የሀገር ውስጥ ዜና

የሴኔጋል ፕሬዚደንት ማኪ ሳል ነገ በሚደረገው የአዲስ መንግስት ምስረታ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

October 03, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፕሬዚደንቱ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ፣ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሀም በላይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በነገው የመንግስት ምስረታ ለመታደም የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም በቀጣይ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!